👉ተማሪዎች #በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆነው እንደሚማሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጸዋል
በዋግኽምራ የሚገኙ የዳስ ትምህርት ቤቶችን ደረጃውን ወደ ጠበቁ መማሪያ ክፍሎች ለመቀየር እየተሰራ ነው 👉የዞኑ ትምህርት መምሪያ
ጥር 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን የሚገኙ የዳስ ትምህርት ቤቶችን ደረጃቸውን ወደ ጠበቁ መማሪያ ክፍሎች ለመቀየር ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በሶስት ዞኖች ተማሪዎች በዳስ ውስጥ እንደሚማሩ የዞኑ የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይፉ ሞገስ ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው በዳስ ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎችን ደረጃቸውን ወደ ጠበቁ ክፍሎች ለማዘዋወር ከሚመለከታቸው አጋር ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎቹ በሌሎች አካባቢ ካሉ ተማሪዎች ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ድጋፍ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ጠቁመዋል፡፡
ዞኑ በሰሜኑ ጦርነት እንዲሁም አሁን በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት የትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ያስታወቁት ኃላፊው፤ ይህ ችግር በተማሪዎች ውጤት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ የማይቀር ነው ብለዋል፡፡
በዋግኽምራ ዞን ተማሪዎችን በትምህርታቸው ብቁ ለማድረግ ቤተ መፅሀፍቶች፣ ቤተ ሙከራዎችና ሌሎችም ግብዓአቶች የሚያስፈልጉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ ችግሩ እንዲፈታ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
#wagihemra #ዋግኽምራ #ዳስ #ትምህርትቤቶችን #ትምህርት #አማራክልል #አስተዳደር
ምላሽ ይስጡ