በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ80 ዓመት አዛውንት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ተገለጸ፡፡
ወንጀሉ የተፈፀመው ህዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ ሚችሌ ሆለና አካባቢ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ተከሳሽ ወጣት ቶሎሳ ዘውዴ የተባለው ግለሰብ ከምሽቱ 6 ሰዓት ላይ የ 80 ዓመት አዛውንት ብቻቸውን ሚኖሩበትን መኖሪያ ቤት ሰብሮ በመግባት ድርጊቱን መፈፀሙ ተነግሯል፡፡
የወረዳው ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አዉሎ ወንጀሉ መፈፀሙን የሚያስረዱ የሰውና የሠነድ ማስረጃዎችን አደራጅቶ ለዐቃቤ ህግ በማቅረብ፤ዐቃቤ ህግ ተከሳሹ አዛውንቷ በቤቷ ለብቻ እንደምትኖር አውቀው ቤት ሰብሮ በመግባት መከላከል በማትችልበት ሁኔታ ድርጊቱን እንደፈፀመ የሚያስረዱ ማስረጃዎች አስደግፎ ለዲላ ዙሪያ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክሱን ማቅረቡን መናኸሪያ ሬዲዮ ከዞኑ ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ማስረጃ የተመለከተው የዲላ ዙሪያ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ተከሳሽ ወጣት ቶሎሳ ዘውዴ የተባለው ግለሰብ የፈፀመውን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ድርጊት በምስክር እና በህክምና ማስረጃ በማረጋገጥ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ