ጥር 14 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ጥር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ቅዳሜ ምሽት ላይ 35 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከየመናዊ ካፒቴን እና ረዳት ካፒቴን ጋር የያዘች ጀልባ ከጂቡቲ ተነስታ በባኒ አል-ሃካም ከተማ አል-ሃጃጃህ አቅራቢያ መስጠሟን በየመን የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።
በአደጋው የዘጠኝ ሴቶች እና የአስራ አንድ ወንዶች ህይወት በድምሩ የ20 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ህይወት አልፏል። ከአደጋው የቀሩት 15 ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የየመን የበረራ ሰራተኞች መትረፍ ችለዋል።
አክሎም ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል በርካታ ጥረቶች ቢደረጉም፣ እ.ኤ.አ. በ2024 ብቻ ከ60,000 በላይ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች ወደ የመን ደርሰዋል ነው የተባለው፡፡
ኤምባሲው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በርካታ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞችን በየጊዜው ከጂቡቲ ወደ አገር ቤት የመመለስ ስራ እየሰራ ቢሆንም በህገ-ወጥ ስደት ምክንያት የበርካታ ዜጎቻችን አካል ከማጉደሉም በላይ የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ የጅቡቲ ኢምባሲ አስታውቋል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ እና የሚመለከተው መንግስታዊ አካል በሙሉ ይህን ህገ-ወጥ ተግባር ለመከላከል እና የዜጎች ህይወት ለመታደግ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ