ጥር 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢትዮጵያ እየተፈጠሩ ያሉ አለመግባበቶችን ለመቅረፍ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰፊ ስራን እየሰራ ቢሆንም ተጨማሪ አጋዥ እንደሚያስፈልገው በሁለተኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም የውይይት መድረክ “ብሄራዊ መግባባት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና ” በሚል ርዕስ እየተካሄደ ባለው የውይይት መድረክ ላይ ተጠቁሟል፡፡
በሃገር ደረጃ ሰፊ የማይታረቁ ሃሳቦች በመኖራቸው በቅድሚያ እነሱን ለማስታረቅ እንዲቻል ለኮሚሽኑ ድጋፍ እንደሚስፈልገው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል፡፡
የማይታረቁ ሃሳቦች መኖራቸው እየተሰራ ባለው ስራ ላይ ከፍተኛ እቅፋት እንደሆኑ የሚናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ቅድሚያ የሚሰጠው ላይ በመግባባት የሃገርን ሰላም ለማስፈን ሊሰራ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በሃገር አቀፍ ደረጃ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ያሉ ክፍተቶችን ማሻሻል ካልተቻለ አሁንም ግጭት ቀስቃሽ ነገሮች እንደማይጠፉ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ መግባባት የለም ማለት አይቻልም መግባባቱን ለማጠናከር ተጨማሪ እሴቶችን ማካተት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
የሃገራዊ ምክክሩና መግባባቱ እንዲሳካ ሁሉ አቃፊነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ