ስኬታማ የቢዝነስ ሰው እና የክለብ ፕሬዚዳንት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ሮድሪጌዝ ለተጨማሪ 4 አመት የማድሪድ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚያገለግሉ በፊርማቸው አረጋግጠዋል።
ለፉክክር ማንም በእጩነት ባልቀረበበት መልኩ ፍፁም ነፃ ሆነው ብቻቸውን ተወዳድረው ነው የተመረጡት ይህም ለ7ኛ ጊዜ በፕሬዚዳንትነት ክለቡን እንዲመሩ ያስችላቸዋል።
ራምን ሜንዶዛይ እኤአ ከ2000 በመርታት ከዛ ጊዜ አንስቶ ይህንን ክለብ በፕሬዚዳንት መምራታቸው አይዘነጋም። 2006 ላይ ስልጣናቸውን ቢያስረክቡም 2009 ላይ በድጋሜ የክለቡን የገቢ ምንጫ የሚያሳድግ ፕሮፖዛል በመንደፍ ዳግም በፕሬዚዳንት መመረጥ መቻላቸው አይዘነጋም ከዛን ወዲህ እስካሁን ድረስ ቡድኑን በፕሬዚዳንትነት እየመሩ ይገኛሉ።
በእግር ኳስ በጣም ትልቅ ተፅእኖ ፈጣሪ ከሆኑ ግለሰቦች እና ጥራት ባለው የአመራርነት ክህሎታቸው ይታወቃሉ። አወዛጋቢው የሱፐር ሊግ እንዲመሰረት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ከሰሞኑ መነጋገሪያ ርዕስ የሆኑ ግለሰብ መሆናቸው አይዘነጋም።
በእሱ ፕሬዚዳንታዊ የአመራርነት ስርአት በእግርኳስ እና ቅርጫት ኳስ ላይ ቡድኑ 65 የዋንጫ ክብሮችን ማሳካት ችሏል። ይህም ከክለቡ አንጋፋ ፕሬዚዳንት እና የስቴዲየማቸው ስያሜ ከሆነው ሳንቲያጎ ቤርናቦ የተሻሉ ክብሮችን ቡድኑ እንዲያሳካ እና ስኬቶችን እንዲጎናፀፍ የፍሎሬንቲኖ ፕሬዝ ጥራት ያለው የአመራር ክህሎት ለክለቡ የጀርባ አጥንት እና ለክለቡ ህልውና ወሳኝ ነገር መሆኑ ማሳያ ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ