ጥር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለካንሰር ህሙማን አገልግሎት ከሚሰጥባቸው ህክምናዎች አንዱ የጨረር ህክምና መሆኑን ተከትሎ በማሽን ብልሽት ምክንያት አጋጥሞ የነበረውን የጨረር ህክምና የአገልግሎት መስተጓጎልና የታካሚ መጉላላት ችግር እየተቀረፈ መሆኑን ሆስፒታሉ አስታዉቋል፡፡
በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በአዲስ አበባ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተጠባባቂ ክሊኒካል ሰርቪስ ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱራዛቅ አህመድ በሆስፒታሉ ከሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች በርካታ ታካሚዎች በየጊዜው በካንሰር ህመም ምክንያት ወደ ተቋሙ እንደሚመጡና ህክምና እንደሚያገኙ ገልጸዋል፡፡ ከህክምናዎቹ አንዱ የጨረር ህክምና እንደመሆኑ በሆስፒታሉ ይሰጥ የነበረው የጨረር ህክምና በማሽን ብልሽት ምክንያት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ እንደነበር በዚህም ምክንያት በወረፋ ሲጠባበቂ የነበሩ ታካሚዎች መጉላላት እንደገጠማቸዉ ተናግረዋል፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት የተኝቶ ማከሚያ ቦታ እጥረት እና ከነበረው የመሳሪያ እጥረት አንጻር አሁን ላይ መሻሻል ተደርጓል ያሉ ሲሆን አሁን ላይ በሆስፒታሉ ዘመናዊ የሆኑ ማሽኖች ተተክለዋል የሚሉት ዳይሬክተሩ ፤ በቅርቡ ከጤና ሚኒስቴርና ከተለያዩ በጎ አድራጊ ተቋማት ጋር በመተባበር አዲስ የተለገሠ የጨረር ህክምና መስጫ ማሽን መገጠሙንና ወደስራ ለመግባት ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው አዲስ የተገጠመው መሳሪያ ወደ ስራ ሲገባ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል እንዲሁም አሁንም ያልተቀረፈውን የታካሚ መጉላላት ለመቀነስ እንደሚያስችልም አስረድተዋል።
ከስራው ጫና እና አሁን ላይ ካለው የታካሚ ብዛት አንጻር አሁንም በርካታ ስራዎች ይቀራሉ የሚሉት ዳይሬክተሩ፤ ሆስፒታሉ ከኮሌጁ ጋር በመተባበር በተሻለ መልኩ የህክምና አሰጣጡን ለማሻሻል ና ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ