ጥር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶች እየተበራከቱ መምጣታቸዉን የሚያመላክቱ መረጃ እና ሪፖርቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ አካላት ወደ ፍትህ ተቋማት በማቅናት ጉዳዩን ለህግ አካል ማሳወቅ ላይ ውስንነቶች እንደሚታዩባቸዉ በተደረጉ ግኝቶች ታዉቋል ሲል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
በኮሚሽኑ የሴቶች ህጻናት አካል ጉዳተኞች እንዲሁም የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሃዋሪያ ፤ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ሴቶች እንዲሁም ህጻናቶች በሚመለከት የወንጀል አስተዳደር ሁኔቴ ውስጥ እየተደረጉ ያሉ አሰራሮችን በሚመለከት ኮሚሽኑ ክትትሎች ስለማድረጉ አስታዉቀዋል፡፡
በዚህም በተደረጉ ክትትሎች አማካኝነት ፍትህ ለማግኘት የሚሄዱ ተጠቂዎች ተግዳሮቶች እየገጠሟቸው እንደሆነ አስረድተው፤ ከፍትህ አካላት የሚሰጠዉ ምላሽ ሪፖርት ካደረጉ በኃላ ከጥቃት አድራሾቹ የሚበረታባቸዉ ጥቃት እና ሌሎችንም ግኝቶች ዘርዝረዋል፡፡
አያይዘውም አሁንም ድረስ ተጎጂዎች እየደረሰባቸው ካለው ጥቃት ባሻገር ለዳግም ጥቃት የመጋላጥ አድላቸው አስጊ እየሆነ መምጣቱን ገልጸው ፤በተለይም በአመለካከት ፤በማሸማቀቅ እንዲሁም በመሰል ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች ዳግም ሰለባ ዉስጥ መሆናቸዉ ተናግረዋል፡፡ የጥቃት ሰለባ እና ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ወደ ህግ አካላት እያቀኑ አለመሆን ፤ የወንጀል ፍትህ አስተዳደሩ ምቹ አለመሆኑን እንዲሁም የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተቋማት በተቋቋሙለት አላማ እየሰሩ ስላልሆነ ችግሩን ዉስብስብ እንዳደረገዉ አስረድተዋል፡፡
የኢፌደሪ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች እና ህጻናትን ጥቃት በመከላከል ረገድ ዋነኛ ሃላፊነት ያለበት ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ መላኩ ባዬ እንደሚሉት ተጎጂዎች በማህበረሰቡ በኩል የተቀመጡ ኃላ ቀር አስተሳሰቦች ወደ ፊት መውጣት እንዳይችሉ እያደረጋቸው እንደሆነ አንስተዉ፡ አሁን ላይ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ቢኖሩም አጥጋቢ አለመሆናቸው እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስቀመጣቸው አሰራሮች የማይከተሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በመኖራቸው ጉዳዩን አሳሳቢ እንዳደረገዉ ገልጸዋል፡፡
ጥቃቶች መቀነስ ከሚቻልባቸዉ መንገዶች መካከል አጥፊዎች ተገቢዉን ቅጣት እንዲያገኙ ማስቻል በመሆኑ ግንዛቤ ማስፋት እና የፍትህ ተቋማት አመቺ እንዲሆኑ አድርጎ ማመቻቸት ላይ ሊሰራበት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ