ጥር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከፍተኛ ድምቀት ከሚከበሩ የአደባባይ ክብረ በዓላት መካከል አንዱ የጥምቀት በዓል መሆኑን ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ አልፏል።
በከፍተኛ ድምቀት ከሚከበርባቸዉ ቦታዎች አንዱ የጎንደር ከተማ ነዉ። 1 ሚሊየን የሚሆኑ የሀገር ውስጥ እንዲሁም የውጭ ታዳሚያኖች በስፍራው ስለመገኘቷቸው ያስታወቀው የጎንደር ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ነው።
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የቢሮው ተወካይ አቶ ልዕልና አበበ በዓሉን ለመታደም ከተለያዩ የአለም ክፍሎች ኢትዮጵያዉያን እና የሌላ ሃገራት ዜጎች በዓሉን ለመታደም መምጣታቸዉን ገልጸዋል።
በተቻለ መጠን ጎብኚዎች በቂ የሆነ የማረፊያ ስፍራ ስለማግኘታቸው ጠቁመው፤ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ወደ ጎንደር የመጡ ዜጎች በቂ የአየር ትራንስፖርት ማግኘት በመቻላቸው ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ማግኘት እንደተቻለም ነው ያመላከቱት።
አያይዘውም በከተማዋ ባለፉት ጊዜያት እድሳት ሲያደርግ የቆየው የአፄ ፋሲለ ደስ ቤተመንግስት ለጉብኝት ክፍት በመሆኑ እንዲሁም በከተማዋ ያለው የልማት እንቅስቃሴ በፍጥነት መሰራቱን ተከትሎ መፋጠኑን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ታዳሚ በከተማዋ መገኘቱን ተናግረዋል።
ካለፉት አመታት ጋር ሲነጻጸር በከተማዋ የተገኘው የታዳሚያኖች ቁጥር መሻሻሎችን ያሳየ በመሆኑ ለተዳከመዉ የቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃትን ፈጥሯል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በማይዳሰሱ ቅርሶቿ መካከል የጥምቀት በዓል አንዱ ሲሆን የ2017 ዓ.ም የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በደማቅ ሁኔታ ተከብረዉ አልፈዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ