ጥር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የ32 አመቱ ግብፃዊው ኮኮብ ሞሀመድ ሳላህ እስካሁን በኮንትራቱ ጉዳይ አዲስ ነገር እንደሌለ እና ለሱ ይሄ በሊቨርፑል ማልያ የሚያሳልፈው የመጨረሻው የውድድር ዘመኑ እንደሆነ እንደሚያምን በተደጋጋሚ መናገሩ አይዘነጋም።
ሞ ሳላህ አምና ማለትም በ2023 ነሀሴ ወር ላይ ከአል ኢትሀድ በጣም የተጋነነ የዝውውር ሂሳብ የ150 ሚሊዮን ፓውንድ ጥያቄ ቀርቦለት የርገን ክሎፕ ተጫዋቹ ለሽያጭ እንደማይቀርብ በመናገር ዝውውሩን ሳያከናውን መቅረቱ አይዘነጋም።
የባህረ ሰላጤዋ ሀገር ሳውዲ ሊግ እየተነቃቃ እንደሚገኝ ይታወቃል። ለዚ ማሳያው እጅግ አይን አዋጅ በሆነ ዝውውር ብራዚላዊው ኮኮብ ኔይማር ጁኒየርን ከPSG ማስፈረማቸው ይጠቀሳል። ግን ተጫዋቹ ለክለቡም ሆነ ለአህጉሪቱ በተለይ የታሰበውን ያህል ተፆእኖ መፍጠር ያቃተው እና በጉዳት ምክንያት በርካታ ጨዋታዎች ላይ አለመሰለፉ አይዘነጋም። እስካሁን ብቻ 3 ጨዋታዎች ላይ ብቻ ተሰልፎ የታሰበውን ያህል ግልጋሎት ሳይሰጥ ወደ 82 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ ማድረጉ ሲገለፆ ቆይቷል።
የኔይማር ጁኒየር ኮንትራት የፊታችን ክረምት የዝውውር መስኮት የሚጠናቀቅ ይሆናል። የሞ ሳላህም ኮንትራት የፊታችን ክረምት
ይጠናቀቃል ስለዚህ ተጫዋቹን ለማስፈረም ከወዲሁ እንቀስቃሴ ስለመጀመራቸው የስካይ ስፖርቱ ጋዜጠኛ ኮቬይ ሶልሄከኮል አሳውቋል።
በ2025 በአሜሪካ በአዲስ የአጨዋወት መንገድ እና ቅርፆ በሚከናወነው የክለቦች የአለም ዋንጫ ላይ ሞ ሳላህ የአል ሂላሎች የፊት ገፆ እንዲሆንም ተፈልጓል። የሳውዲ ሻምፒዮኖቹ አል ሂላሎች ይህ እውን እንዲሆን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ላይ ናቸው።
የሞ ሳላህ ወኪል ራሚ አባስ በዚ ሰአት ከሳውዲ አመራሮች ጋር ንግግር ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
የሳውዲ አረቢያ የመዝናኛ ዘርፍ ዋና ሀላፊ የሆነው ተርኪ አላልሺክ ይሄ ግለሰብ ሳውዲ በእግርኳስ ብቻም ሳይሆን ቦክስ ፤ UFC እና Fotmula 1 አሉ የተባሉ ተጠባቂ ውድድሮች መናኸሪያቸው ሪያድ ከተማ እንዲሆን በማድረግ ትልቁን ሚና እየተወጣ የሚገኝ ግለሰብ ነው።
ከሀገሪቱ መሪ መሀመድ ቢን ሳልማን ጋር ያለው ቅርበህ ይታወቃል። ታዲያ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ሞ ሳላህን በአል ሂላል ማልያ የተቀነባበረ ፎቶ ማጋራቱ መነጋገሪያ ሆኗል።
የፊታችን ነሀሴ ወር ግብፃዊው ኮኮብ ሞ-ሳላህ 33 አመቱን ይይዛል። አሁንም በትልቁ መድረክ ማለትም በአውሮፓ ትልልቅ ሊጎች ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችል አቅም እንዳለው ቢያምንም የሳውዲ ጥያቄንም ለመቀበል ዝግጁ እንደሚሆን ሶልሄኮል በመረጃው ላይ ያሰፈረው ፆሁፍ ያመላክታል።
ሞ ሳላህ ስለ ኮንትራቱ ጉዳይ በቅርብ ተጠይቆ ምንም አዲስ ነገር የለም ፤ በክለቡ የመጨረሻ አመቴ ላይ ነው የምገኘው ሲል ሀሳብ መስጠቱ አይዘነጋም።
በሚካኤል ደጀኔ
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ