ጥር 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን የከተማዋን የትራፊክ መብራቶች ባልተቆራረጠ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ 27 የትራፊክ መብራት ባሉባቸው ቦታዎች ለይ የሶላር ሃይል መቀበያ መሳሪያ መትከሉን አስታውቋል።
በባለስልጣን መ/ቤቱ የመንገድ ደህንነት ምህንድስና ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዘይኑ ኤልያስ እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል በኤሌክትሪክ መቆራረጥ ሳቢያ የትራፊክ መብራቶች ያለመስራት ችግር እንደሚገጥም እና ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ ባለፉት ስድስት ወራት የትራፊክ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ በጸሀይ ሃይል የሚሰራ የሃይል አቅርቦት እንዲኖር መደረጉን ገልጸዋል።
በጸሃይ ሃይል የሚሰሩ የሀይል አቅርቦት የተተከለባቸው ቦታዎችም ጀርመን አደባባይ፣ ጀሞ ሚካኤል፣1 አየር ጤና፣ 18 ማዞሪያ፣ 3 ቁጥር ማዞሪያ፣ ጦርሃይሎች. ለገሀር፣ እስጢፋኖስ፣ ቅዱስ ዮሴፍ፣ ብሄራዊ ትያትር፣ ኢቲቪ/ፖስታ ቤት/፣ ጥቁር አንበሳ፣ ሰንጋተራ፣ ባንኮዲሮማ፣ ፓርላማ፣ አትላስ፣ ቦሌ ሚካኤል፣ አፍሪካ ህብረት፣ ትምባሆ፣ ሾላ ገበያ፣ ሾላ ፔፕሲ፤ ሳህሊተማርያም. ቦሌ ሚሊኒየም፣ ቦሌ ሱፐር ማርኬት መሆናቸውን አቶ ዘይኑ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም የሶላር ሃይል አቅርቦት በጥናት እየተለየ መሳሪያው የሚተከል መሆኑን የገለጹት አቶ ዘይኑ አዲሶቹ የትራፊክ መብራት ተከላዎችን ጨመሮ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ 90 ቦታዎች የትራፊክ መብራት እንዳለና የትራፊክ ፍሰቱም ሰላማዊ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ