
ጥር 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባሳለፍነው አመት በሃገራችን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪዎች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል መባሉን ተከትሎ በኮንትሮባንድ እና በህግ ሽፋን አማካኝነት ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ የብረታ ብረት ምርቶችን ለመቆጣጠር የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ምን እየሰራ ነው ሲል መናኸሪያ ሬዲዮ ጠይቋል ።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ በመምላሻቸው እንደገለጹት በሃገራችን የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት የሚቀንሱ በኮንትሮባንድ የሚገቡ ምርቶችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በኮንትሮባንድ እና ህግን ሽፋን ባደረገ መልኩ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች፤ የሃገራችን ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን የሚቀንሱ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን የሚፈጥሩ በመሆናቸው በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር የሚመራ ግብረ ሃይል በማቋቋም በክልል እና በከተማ ያለውን የኮንትሮባንድ ንግድ በመቆጣጠር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የብረታ ብረት ኢንዱስትሪውን ጨምሮ አጠቃላይ የሃገሪቷን ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ የሆኑ ኢንደስትሪዎችን ከኮንትሮባንድ እና ከህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ ነው ሲሉ አስረድተዋል ።
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ጉዳዩ የመንግስት ብቻ ባለመሆኑ ህብረተሰቡ ማንኛውንም ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የማጋለጥ ሃላፊነት አለበት ሲሉ አመላክተዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ