ጥር 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተቋማት በተለያዩ ጉዳዮች የሚያወጧቸዉን ሪፖርቶች ፖሊሲዎችን ለመፈተሽና ለፖሊሲ ግብዓትነት እየተጠቀምኩባቸዉ ነዉ ሲል የኢትዮጵያ ፖሊሰ ጥናት ኢንስቲትዩት ቢገልጽም ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር በተገናኘ ግን ባለፉት ሁለት አመታት ጥናት አለማድረጉን ገልጿል፡፡
ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ የሰብዓዊ መብት አያያዝ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጥናቶች በሪፖርት ይፋ ሲደረጉ ቢታይም በግብዓትነት ተቀብሎ መፍትሄ የሚሰጥባቸዉ አካል እንደሌለ ይገለጻል፡፡
በተለይም በሰብዓዊ መብተቶች ላይ መሰረታቸውን በማድረግ ሪፖርቶችን የሚያወጡ ተቋማት በርካታ ቢሆኑም የሚያወጧቸው ሪፖርቶች ከሪፖርትነት ባሻገር ተፈጻሚነት ላይ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉባቸው ተቋማቱ በተደጋጋሚ ቢያነሱም የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከተቋማት የሚወጡ ሪፖርቶችን መነሻ በማድረግ የፖሊሲ ጥናት እያካሄድኩባቸዉ ነዉ ሲል ገልጿል፡፡
በኢንስቲትዩቱ የብዝሃነት አስተዳደር እና የህግ የበላይነት የጥናት አስተባባሪ ዶ/ር ሙሉጌታ ጌጡ ዲሞክራሲያዊ በሆኑ ተቋማት በኩል የሚወጡ ሪፖርቶች ዋቢ በማድረግ ጥናት እና ምርምሮች እየተደረጉ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በየጊዜዉ በሚያወጣቸዉ ሪፖርቶች የፖሊሲ እና የህግ ከፍተቶች እንዳሉ ሲጠቅስ ይስተዋላል፤ እነዚህን ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ የምርምር እና የማሻሺያ ስራዎች ምን ያህል ተሰርተዋል የሚለዉን ለዶክተር ሙሉጌታ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
የፖሊስ ጥናት ኢንስቲትዩት እስካሁን ድረስ በሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት እና ሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ያደረጋቸው የጥናት እንዲሁም የምርምር ስራዎች ባይኖሩም በተለየ መልኩ ግጭቶች እንዲሁም በማህበረሰቡ ውስጥ አናሳ ቁጥር ያላቸዉ #ህዳጣን ተብለው ለተሰየሙ ዜጎች መብቶቻቸውን እንዳይነፈጉ በማድረግ ውስጥ የተሰሩ ጥናቶች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ ሆኖም ግን ባለፉት 2 ዓመታት ከሰብዓዊ መብት ጋር የተገናኘ ጥናት በኢንስቲትዩቱ አለመደረጉን ተናግረዋል፡፡
አሁንም ድረስ ተቋማት በርካታ ሪፖርቶችን የሚያወጡ ቢሆንም እነዚህን ሪፖርቶች ወስዶ ለግብዓትነት መጠቀም ላይ ከፍተኛ ክፍተት እንደሚስተዋል ይገለጻል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ