ጥር 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስር ከሚገኙ አምስት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነዉን የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ራስ ገዝ የማድረግ የስራ ሂደት በተግባር አለመጀመሩ ተገለጸ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ሁንዴሳ ለመናኸሪያ ሬዲዮ እንደገለጹት፤ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ራስ ገዝ የማድረግ ስራ ከንድፈ ሃሳብ ባለፈ የተግባር ስራ አልተጀመረም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ተግባራዊ የማድረግ ሂደቱ ዘግይቷል ያሉት ሃላፊዉ የዘገየበት ዋነኛ ምክንያት የጤና ሳይንስ ኮሌጁ የራሱን መዋቅር እንዲኖረዉ የንድፈ ሃሳብ ስራ ሲሰራ በመቆየቱ ነዉ ብለዋል፡፡
ኮሌጁን ሙሉ ለሙሉ ራስ ገዝ የማድረግ ስራው ወደ ተግባር ሲገባ ትልልቅ የሆኑ የመንግስት ሆስፒታሎች ላይ ያለዉ የስርዓት ችግር ላይ ያተኮረ የመልሶ ማቋቋም ስራ እንደሚሰራ እና የህብረተሰቡን ጥያቄ በመመለስ ተገልጋይ ተኮር የሆነ አገልግሎት ማህበረሰቡ እንዲያገኝ ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጤና ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር ስር ሆኖ ራስ ገዝ የመሆን ሂደቱን እንደሚያስቀጥል አመላክተው የመማር ማስተማር ሂደቱን ከማሻሻል ባለፈ የክፍያ ስራቱን በማሻሻል ምቹ የስራ ሁኔታን ለመፍጠር በእቅድ ደረጃ መያዙን ጠቁመዋል፡፡
ባሳለፍነው ዓመት የጤና ሚኒስቴር ጥቁር አንበሳ ሆስፒታልን ራስ ገዝ የማድረግ ስራ ተጀምሯል የሚል መረጃ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ