ጥር 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሃገር አቀፍ ደረጃ ለ12ኛ ጊዜ የተዘጋጀው የጥራት ውድድር በይፋ ጥር 5 2017 ዓ.ም በተሳታፊዎች ምዝገባ መጀመሩ ተገልጿል፡፡ የሽልማቱ ዓላማ ማወዳደር እና መሸለም ብቻ ሳይሆን ያሉትን ክፍተቶች በትብብር ለይቶ ለመፍታት ነዉ ያለዉ የኢትዮጵያ ጥራት እና ሽልማት ድርጅት ነዉ፡፡
አንድ ወር ከ10 ቀን የጊዜ ገደብ የተቀመጠለት የምዝገባ ሂደቱ 50 ተቋማትን ብቻ በውድድሩ ተሳታፊ የማድረግ ስራ የሚሰራ ቢሆንም ይሄን ያህል ጊዜ የተሰጠውም አገልግሎት ሰጪ የሆኑ አምራች ተቋማት በሃገር አቀፍ ደርጃ የሚዘጋጁትን ውድድሮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ስለማይኖራቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ጥራት እና ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ መብራሃቱ ገልጸዋል።
በህጋዊ መንገድ የሚደረጉት ውድድሮች የሚኖራቸው መስፈርቶች ከፍተኛ በመሆኑ ብዙ ተቋማት በዚህ መንገድ ማለፍ አይፈልጉም ያሉ ሲሆን ከዚያ ይልቅ ግን ለትርፍ በተቋቋሙ ሃሰተኛ እና የተምታታ ስራ በሚሰሩ አካላት የሚደረጉ ሽልማቶችን ለማግኘት ይሳተፋሉ ይሄ ሽልማት ደግሞ ለተቋማት ጥራት የሚያበረክተዉ ነገር የለም ሲሉም አስረድተዋል፡፡
የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና በግል ዘርፍ ላይ በተሰማሩ አካላት የተዋቀረ ቦርድ ያለው ድርጅቱ ጥር 03 ቀን 2017 ዓ.ም በነበረው ስብሰባ ላይ ያሉትን ችግሮች እና የመፍትሄ አቅጣጫ ላይ መክሯል፡፡
ተሳታፊዎች በጥራት ጉዳይ ላይ ትልቁን ድርሻ እንደመውሰዳቸው ወደፊት ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ዉድድር ብቻ ሳይሆን ፤አስገዳጅ ሁኔታ ተቀምጦ በተቋማት ምርታማነት ብሎም ሃገራዊ እድገት ላይ ውሳኝ ሚና የሚኖረዉ የዉድድር ሂደት እንደሚኖር የኢትዮጵያ ጥራት እና ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ መብራሃቱ ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ