ጥር 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) እሳተ ገሞራና የመሬት መንቀጥቀጥን የመሳሰሉ ድንገተኛ የተፈጥሮ አደጋዎችን ሁነት በምስል ለማስቀረት እና ለመመልከት ወደ ስፍራው የሚያቀኑ አካላት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የስነ- ምድር መምህሩ አሊ ሙሳ ለመናኸሪያ ሬድዩ እንደገለጹት፤ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታና የመሬት መንቀጥቀጥ ከአፋር ክልል አልፎ ወደ ሌሎቹ ክልሎች በተስፋፋበት ወቅት አንዳንድ ግለሰቦች ምንም አይነት ጥናት ባልተደረገበት አካባቢ ሁነቱን ለመቅረጽ ወደ ስፍራው ማቅናት እንደሌለባቸው አመላክተዋል፡፡
የሚመለከታቸው አካላትም ለማህበረሰቡ ስለጉዳዩ በቂ መረጃ ተደራሽ ማድረግ እንዳለባቸው የተናገሩት መምህሩ፤ አደጋው መቼ እና እንዴት እንደሚከሰት ስለማይታወቅ ክልሉ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ላይ ጎብኚዎች እንዳይሄዱ መከልከል አለበት ብለዋል፡፡
የተፈጥሮ ክስተቱ ባለበት አከባቢ መቅረብ ካስፈለገም በባለሞያ እና በመሳሪያ በመታገዝ መሆን እንዳለበት የሚገልጹት ደግሞ ሌላኛው የስነ ምህዳር ባለሙያ አቶ አያና አላምር ናቸው፡፡ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችም ሆኑ ሌሎች የማሳወቅ ስራ መስራታቸው በጥሩ ጎኑ የሚታይ ቢሆንም ያለምንም የባለሙያ ጥናት ቦታው ላይ መሄድና ከፍንዳታው የሚወጣውን ውሃ መጠቀም ተገቢ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡
የተፈጥሮ አደጋ በሚያጋጥምባቸው አከባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አካላት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ተገልጿል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ