ጥር 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ መቶ የሚሆኑ አዳዲስ የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ከአንድ ወር በኋላ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በርኦ ሀሰን እንደገለጹት፤ የመዲናዋን የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር ለመፍታትና አረንጓዴ ትራንስፖርት ስትራቴጂን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ አንድ መቶ የኤሌክትሪክ አውቶብሶች ገብተው እየተገጣጠሙ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ከአንድ ወር በኋላም አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹ ሲሆን የኤሌክትሪክ አውቶብሶች በብዛት እንዲገቡ እየተሰራ እንደሆነና ከ15 መቀመጫ በላይ ያላቸው ሚዲባሶችም ገብተው የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ