👉ኢትዮጵያ አምባሳደሯን ወደ መቃዲሹ እንደምትልክ የተገለጸ ሲሆን፤ ሶማሊያም እንዲሁ አዲስ አምባሳደር ወደ አዲስ አበባ ትልካለች ተብሏል።
ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ኦማር ባልሳድ በሀገራቸው በኩል የውሳኔ ለውጥ መኖሩን አመልክተው፤ ከዚህ ውሳኔ አስቀድሞ ሌሎች ሃገራት የወታደር አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ በመጠየቃቸው አዳጋች ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል መግለጻቸው ተጠቁሟል፡፡
ኢትዮጵያ በዚህ የሕብረቱ የሶማሊያ ተልእኮ ውስጥ እንዳትካተት እንቅፋት የነበረው ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችው የመግባቢያ ሰነድ እንደሆነና ያ ርዕሰ ጉዳይ መፍትሄ አግኝቷል ማግኘቱን አስታውቀዋል፡፡
አያይዘውም የሚፈለገው የወታደር መጠን በአብዛኛው በሌሎች ሃገራት በመሸፈኑ፤ ቀሪውን ትንሽ ቁጥር የማከፋፈሉ ጉዳይ ዋና ፈተና እንደሆነባቸው ገልጸዋል ነው የተባለው፡፡
ለዚህም መፍትሄ ለማግኘት በንቃት እየሠሩ መሆኑን ጠቁመው፤ የሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያን መፈራረም ተከትሎ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከግዛቷ እንዲወጡ ደጋግማ መጠየቋን ተከትሎ ግብፅ ፈጠን ብላ በዚህ ተልዕኮ ሥር ወታደሮቿን ለማሰማራት ዝግጁ መሆኗን አሳውቃ፤ ከመቃዲሹም ይሁንታ ማግኘቷ አይዘነጋም።
በአዲሱ የአፍሪቃ ሕብረት የሶማሊያ ተልዕኮ ሥር ወታደሮችን የሚያሰማሩት ሃገራት እስካሁን ዝርዝራቸው ይፋ አለመሆኑ ይታወቃል፡፡ አያይዘውም፤የሶማሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ በቅርቡ በሶማሊያ አምባሳደሯን ወደ መቃዲሹ እንደምትልክ የገለጹ ሲሆን፤ ሶማሊያም እንዲሁ አዲስ አምባሳደር ወደ አዲስ አበባ ትልካለች ማለታቸውን ዶቼቨሌ ዘግቧል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ