ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የቁጥጥር ፎረም በመመስረት የተለያዩ ህገወጥ ድርጊት ሲፈጽሙ በቆዩ የአገልግሎት ሰጪ እና የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል፡፡
በመዲናዋ ህብረተሰቡን ለአደጋ ሊያጋልጡ የሚችሉ ተግባራትን የፈጸሙ 466 ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የገለጹት በአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን የምግብና ጤና ተቋማት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ናቸው፡፡
በ92ቱ ተቋማት ላይ የማሸግ፣ 2 የዘይት አምራች ድርጅቶች ላይ ደግሞ ከገበያ የማስወጣት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡
በህብረተሰቡ ጥቆማ እና በጸጥታ አካላት በተደረገ አሰሳ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ነው ያብራሩት፡፡
በተለያዩ አማራጮች ቁጥጥር እንደሚደረግ ያስታወቁት ዳይሬክተሩ፤ ተቋማቱ ያለባቸውን ክፍተት እንዲያርሙ እና ለባለስልጣኑ እንዲያሳውቁ የሚደረግበት አሰራር እንዳለም ገልጸዋል፡፡
ህብረተሰቡ ባለስልጣኑ ባዘጋጀው ነጻ የስልክ መስመር 8864 ላይ በመደወል ወይም የጽሁፍ መልእክት በመላክ፤ አሊያም በአካል በመቅረብ ጥቆማ እና ቅሬታ እንዲሰጥ ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ