ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጥቂት የማይባሉ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ አገልግሎት ሰጪ እና አምራች ድርጅቶች ለተቋማቸው መልካም ገጽታ ግንባታ በሚል ግልጽ ባልሆነ የጥራት ምዘና እና ማንነታቸው ባልታወቁ አወዳዳሪ አካላት የሚወስዱት ሽልማት የማጭበርበር ተግባር መሆኑን የኢትዮጵያ ጥራት እና ሽልማት ድርጅት ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጿል።
የማወዳደሪያ መስፈርቱ እና አወዳዳሪዎቹ በማይታወቁበት ሁኔታ እንዲሁም አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ በሚል ያልተገባ ስያሜ በመያዝ የሚሸልሙ ድርጅቶች መኖራቸውን ተቋሙ አመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያም ለንግድ አላማ የተቋቋሙ ሸላሚ ድርጅቶች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ መበራከቱን እና ይህም መሆኑ በምርቶች እና የአገልግሎት ጥራት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በእንዲህ አይነት የማጭበርበር ድርጊት ላይ ከተሳተፉ የመንግስት ተቋማት መካከል የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አንዱ እንደሆነ የኢትዮጵያ ጥራት እና ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴድሮስ መብራቱ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የጥራት እና ሽልማት ድርጅት ለምርቶች እና አገልግሎት ጥራት ተግዳሮት የሚሆነውን ባልተገባ መልኩ የሚከናወን ሽልማት እና ውድድር አዘጋጅ እና ተሳታፊዎችን በህግ አግባብ እንዲጠየቁ የማድረግ ኃላፊነት እንደሌለው አመላክቷል፡፡
ይሁን እንጅ ተቋሙ ከቅርብ አመታት ወዲህ የችግሩን መስፋት ተከትሎ ከሚመለከታቸው የመንግስት ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረበት እንዳለ ነው የኢትዮጵያ ጥራት እና ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ መብራቱ የገለጹት።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ