ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የጥምቀት በዓልን ለማክበር ወደ ጎንደር የሚመጡ ታዳሚዎችን ለመቀበል ከተማዋ ዝግጁ መሆኗን የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው አስታውቀዋል፡፡
በጎንደር በየዓመቱ በድምቀት ለሚከበረው የጥምቀት በዓል ወደ ከተማዋ የሚገቡ ታዳሚዎች በዓሉን በጥሩ ሁኔታ አሳልፈው እንዲመለሱ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ሲሉ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አስታውቀዋል፡፡
ከተማዋ ለመስህብነት የሚውሉ በርካታ ቅርሶች እና አቅሞች ባለቤት መሆኗን ጠቅሰው፤ የበዓሉ ታዳሚዎች እነዚህን መስህቦች መጎብኘት የሚችሉበት አጋጣሚም እንደሆነ ነው የገለጹት።
በአካባቢው የሚስተዋሉትን ግጭቶች በመግታት ዘላቂ ሰላም ለማስፈንም እየተሰራ ስለመሆኑም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ጠቅሰዋል፡፡
ለግጭት መንስኤ የሆኑ ነጥቦች መለየታቸውን እና ከማህበረሰቡ ጋር ለመስራት እንቅስቃሴ መጀመሩንም ጠቁመዋል፡፡
የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር ዝግጁ ናት ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው፤ በዓሉን የሚያከብሩ ወደ ከተማዋ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ