ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ላለፉት 14 አመታት ግድቡን ለማጠናቀቅ ከትውልደ ኢትዮጵያውያን በስጦታ እና በቦንድ ግዢ የተሰበሰበው ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ የግድቡ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ባለፉት ዓመታት ለግድቡ ከተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ አብዛኛው ገንዘብ የተሰበሰበው በቦንድ ሽያጭ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ አስታውቀው፤ በአጠቃላይም ከ20 ቢሊዮን 213 ሚሊዮን ብር በላይ እንደተሰበሰበ ተናግረዋል፡፡
በ2016 በጀት አመት ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ እንደነበር አስታውሰው፤በ2017 በጀት አመት አራት ወር ውስጥ 311 ሚሊዮን ብር እንደተገኘ እና በተያዘው በጀት አመት 1.6 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የግድቡ ግንባታ ከ97 ነጥብ 6 በመቶ በላይ ቢደርስም አሁንም ግድቡን ለማጠናቀቅ የኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንደሚያስፈልግ በአፅዖት ተናግረዋል፡፡
ከሰሞኑን ለግድቡ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ብሔራዊ ባንክ 5 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ሌሎች ሃገር በቀል ድርጅቶች ባደረጉት የቦንድ ግዢ 25 ሚሊዮን 900 ሺህ ብር እንደተገኘ አክለው ገልጸዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ