ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ ጣልያናዊ ለጉዳት በጣም ተጋላጭ የሆነ ተጫዋች መሆኑ በተደጋጋሚ ገና ቦሎኛም እያለ የጉዳት ታሪክ በብዛት ያለበት ተጫዋች መሆኑ ሲገለፆ የቆየ ጉዳይ መሆኑ አይዘነጋም።
ጣልያናዊው የግራ መስመር ተመላላሽ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች መድፈኞቹን ባሳለፍነው ክረምት የዝውውር መስኮት ላይ ከተቀላቀለ ወዲህ በውድድር ዘመኑ እስካሁን 3 ጊዜ ጉዳት እንዳጋጠመው የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ከትላንቱ የኤፍ ኤ ካፕ ጨዋታ ከስብስቡ ውጪ የተደረገው ደግሞ በድጋም የጡንቻ ህመም ስላጋጠመው ነው መባሉ ተጫዋቹ ወጥነት ያለው የሜዳ ላይ ግልጋሎት በቀጣይ ጊዜ ላይስ ይሰጣል ወይ የሚለው ጥያቄ እንዲነሳበት እያደረገው ይገኛል።
ካሊያፊዮሪ ባሳለፍነው መስከረም ወር ላይ ከቶተንሀም ጋር እንዲሁም ጥቅምት ወር በጉልበት ጉዳት ምክንያት ላይ ከሊቨርፑል ጋር የተደረጉ ተጠባቂ ጨዋታዎች ላይ አልተሰለፈም ሀገሩንም በኔሽንስ ሊግ በተለይ ከእስራኤል ጋር የተደረገው ጨዋታ ያለፈው ተጫዋች ነው።
የኖቲንጋም ፎረስት እና ዌስትሀም ጨዋታ ላይ ከተሰለፈ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ ፤ ሼምፒዮኝስ ሊግ እና EFL የካራባኦ ካፕ ጨዋታ በድምሩ 5 ጨዋታ እንዳለፉት የሚታወስ ነው።
ባጠቃላይ ለአርሰናል ተሰልፎ ማድረግ ከነበረበት 31 ጨዋታ 17 ጨዋታዎች ላይ ብቻ ነው ተሰልፎ መጫወት የቻለው። 4ኛው ጉዳቱ ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ ያርቀዋል የሚለው የተገለፀ ጉዳይ ባይኖርም የ22 አመቱ ተጫዋቹ ተደራራቢ ጉዳት በአንድ የውድድር ዘመን ያጋጠመው ተጫዋች መሆኑ ዘለቄታዊ ጠቀሜታው ምን ያህል ነው የሚለው ቀደም ተብሎ እንደተነሳው እየተነሳበት የሚገኘው ጥያቄ ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ