ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል የተአማኒነት ችግርና የክልሉ መንግስት የድጋፍ እጥረት ለስራው ተግዳሮት እንደሆነበት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
ካውንስሉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ የሎጂስቲክ እጥረት እንዳለበት ቢገልጽም፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ የድጋፍ ችግሩ ሳይቆረፍ እንደቀጠለ የካውንስሉ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ እያቸው ተሻለ ለጣቢያችን ገልጸዋል።
ካውንስሉ ባሉት አደረጃጀቶች አማካኝነት ሁለቱን አካላት ለማቀራረብና ለድርድር ለማመቻቸት ቢሞክርም በስራው ሒደት የክልሉ መንግስት ድጋፍ ማድረግ ቢኖርበትም ችላ እንዳለ የሚገልጹት አቶ እያቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ያለው ግጭትም ተንቀሳቅሶ ለመስራት እና ታጣቂ ሃይሎችን ለማናገር ተግዳሮት እንደፈጠረ ተናግረዋል።
የሰላም ካውንስሉ ድርድርን አመቻቺ አካል ሆኖ እየሰራ ቢሆንም በሁለቱም ተዋጊ አካላት ዘንድ እንደማይታመን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ገልጸዋል። የሲቭል ማህበራት ድርጅቶች አጋዥ እንዲሆኑ ቢጠበቅም አሁን ላይ ካውንስሉን የሚያግዙ ድርጅቶች አለመኖራቸውን ነው የገለጹት።
ግጭት ሲያጋጥም ሰላማዊ ድርድሮች እንዲደረጉ እና አዎንታዊ ውጤት እንዲመጣ ከሚሰሩ ተቋማት መካከል መንግስታዊ ያልሆኑ ሀገር በቀል የሲቭል ድርጅቶች ተጠቃሽ ናቸው የሚሉት የቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ፎር ዲሞክራሲ ስራ አስኪያጅ አቶ ታደለ ደርሰ ናቸው።
አሁን ላይ የአማራ ክልል የሰላም ካውንስል ድጋፍ ስለመፈለጉም ሆነ ስለገጠመው ችግር እንደ ድርጅት ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለና ምንም አይነት ጥያቄ እንዳልቀረበላቸው በመጥቀስ ምን ጊዜም ከሰላም ካውንስሉም ሆነ ከመሰል ድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የአማራ ክልል የሰላም ችግር እንዲፈታ ካሁን ቀደም የክልሉን መንግስት ጨምሮ የፌደራል መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ርብርብ እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ