ጥር 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በተለያዩ ዘርፎች ላይ ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ከውጪ በሚገቡ ምርቶች በሃገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች በመሸፈናቸው ከዚህ በፊት ሲወጣ የነበረውን ወጪ ማስቀርት መቻሉ ብሎም ለዜጎች የስራ እድል መፈጠር እንደተቻለ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል።
ለኢንዱስትሪ ግብዓት በመሆን ከሚያገለግሉ ምርቶች ጀምሮ የምግብና አልባሳት በሃገር ውስጥ የመተካት እቅድ ለማሳካት በሃገር ደረጃ የተያዘው ሲሆን ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ደግሞ በተለያዩ ቦታዎች ያሉ ፋብሪካዎች ብሎም የኢንዱስትሪ ፓርኮች በሙሉ አቅማቸው በመጠቀም በሰሩት ስራ የመከላከያ ደምብ ልብስ ሙሉ ለሙሉ በሃገር ውስት ምርት መተካቱን የገለጹት የኢንደስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሐሰን መሃመድ የሃገር ውስጥ አምራችነትን መጨመር እና በተለያዩ ዘርፎች ለዜጎች የስራ እድል የፈጠሩ መሆናቸውን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሃገር ውስጥ ፍላጎትን በሃገር በቀል ደረጃቸውን በጠበቁ እና ጥራት ባላቸው ምርቶች ሙሉ በሙሉ መተካት ብቻም ሳይሆን የውጪ ንግድን ለመጨመር በአዋጅ ፣በህግ እና ደምብ የተቀመጡን በማስፈጸም ማሳካት እንደሚቻል አቶ ሃሰን አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ