ጥር 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባዔ የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል፡፡
በወቅቱም ከምክር ቤቱ አባላት በርካታ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን የቁጥጥር ስርዓቱ ላይ አሁንም ከፍተኛ ክፍተት በመኖሩ ነዳጅ በሚፈለገው ልክ ተጠቃሚው ጋር እየደረሰ አለመሆኑ ተገልጻል፡፡
የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን በበኩሉ በቅርቡ ዘመናዊ የቁጥጥር ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
አሁን ላይ ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች የአድራሻ መቆጣጠሪያ ጂ.ፒ.ኤስ. ተገጥሞላቸው ቁጥጥር እየተደረገ ቢሆንም፤ ነዳጅ ከተራገፈ በኃላ ማድያዎች ነዳጅን በህገ ወጥ መልኩ እየሸጡ በመሆኑ ሌላ ዘመናዊ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ በቅርቡ ነዳጅ ማደያዎች ላይ ተግባራዊ የሚሆን ዘመናዊ አሰራር ለመዘርጋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ማዲያዎች በህገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ሲገኙ የማሸግና ሌሎችም እርምጃዎች እንደሚወሰድባቸው አስታውቀው፤ ይሁን እንጂ በሚፈለገው ልክ መፍትኤ ባለመምጣቱ ዘመናዊ የቁጥጥር ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሁኖ መገኘቱን አብራረተዋል፡፡
መንግስት ካወጣው ተመን በላይ እንዲሁም በህገ ወጥ መልኩ ነዳጅ ሲሸጥ የተገኘ አካል በአዲሱ አዋጅ ከ3 እስከ 7 ዓመት እንዲሁም ከ350ሺ እስከ 500 ሺ ብር መቀጮ እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡
በረቂቅ አዋጁ በተጨማሪነት የቀረቡት ማሻሻያዎች ተካተውበት አዋጅ ቁጥር 1363/2017 ሆኖ በ2 ተቃውሞ እና በ1 ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ