ጥር 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በናይጄሪያ ሰሜናዊ ምስራቅ በናይጄሪያ ጦር እና እስላማዊ መንግስት ምዕራብ አፍሪካ ግዛት መካከል በተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት ምክንያት በሁለቱም ወገኖች ላይ ጉዳት መድረሱን የናይጄሪያ መከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ትላንት በመግለጫው አስታውቋል።
የናይጄሪያ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ጥር 4 ቀን ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ ታጣቂዎች በቦርኖ ግዛት ሳባን ጋሪ መንደር የሰፈሩትን የሰራዊት አባላትን እንደገጠሙ ገልጸዋል። አክለውም በግጭቱ 34 አሸባሪዎች የተገደሉ ሲሆን ስድስት ወታደሮች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል ብለዋል ።
ዘገባዉ እንደገለጸዉ ቦኮ ሃራም እ.ኤ.አ. በመጋቢት 2015 ለ ISIS ታማኝ ሆኖ ለመስራት ቃል መግባቱን አስታዉሷል። እራሱን ምዕራብ አፍሪካ ግዛት እስላማዊ መንግስት ብሎ መሰየሙም ይታወቃል።
ይሁን እንጂ ቡድኑ በኋላ ለሁለት ተከፍሎ ቦኮ ሃራም እና አይኤስዋፕ እንደ ተለያዩ አካላት መንቀሳቀስ መጀመራቸዉን ሻፋቅ ኒዉስ ዘግቧል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ