ጥር 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሜሪካ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል ከሚለው ክስ ባለፈ የቡድኑ መሪ ላይ ማዕቀብ ጥላለች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄሜቲ በመባል የሚታወቁት የቡድኑ መሪ በሱዳን ህዝብ ላይ ለ20 ወራት በዘለቀው ጦርነት በአገሪቱ ዜጎች ላይ ግፍ በመፈጸማቸው እየተቀጡ ነው ብለዋል።
የፈጥኖ ደራሽ ሃይል እና ደጋፊው ታጣቂ ቡድኖች ህጻናት ወንዶችን ሳይቀር በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል፤ ሴቶች ላይም ወሲባዊ ጥቃት ፈጽመዋል ብለዋል።
ታጣቂ ቡድኖቹ ሰላማዊ ዜጎች እና ከግጭት የሚሸሹ ንጹሃንን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈጸማቸውንም ነው የተናገሩት፡፡
አንቶኒዮ ብሊንከን “ባለኝ መረጃ መሰረት አሁን የ RSF አባላት እና አጋር ታጣቂዎች በሱዳን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ” ማለታቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው።
የፈጥኖ ደራሽ ሐይሉ በምላሹ ጦርነቱን ውጤታማ በሆነ መልኩ መፍታት ወይም ማስቆም አልቻለችም ሲል አሜሪካን ወቅሷል፡፡
የሄሜቲ አማካሪ ኤል ባሻ በኤክስ ባጋሩት መልዕክት “ውሳኔው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር የሱዳንን ችግር ለመፍታት አለመቻሉን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ይህም የሱዳንን ቀውስ ከማወሳሰብ ባለፈ የግጭቱን መንስኤዎች ለመፍታት የሚደረገውን ድርድር ሊያደናቅፍ እንደሚችልም አክለዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ