ጥር 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በየቀኑ ከ3 ሚሊየን ሊትር በላይ የቤንዚን ፍላጎት መኖሩን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሀገሪቱ የነዳጅ ፍላጎት አሁን እየገባ ካለው ጋር ተቀራራቢ ቢሆንም ህገወጥ ተግባር በሚፈጽሙ አካላት ምክንያት የአቅርቦት ችግር እንደሚፈጠር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ አብዱላኪም ሙሉ ተናግረዋል።
በሀገሪቱ የነዳጅ ስርጭት እና ግብይት ላይ ከፍተኛ ችግር መኖሩን ነው የገለጹት። ይህን ተግባር በሚፈጽሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑን በመግለጽ፤ ባለፉት 4 ቀናት ብቻ በተደረገ ዳሰሳ ከ95 ማደያዎች 22ቱ ከአሰራር መመሪያ ውጪ ሲተገብሩ ተደርሶባቸዋል ብለዋል።
እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ነዳጅ በሰዓቱ እንዳይገባ ባደረጉ 251 የቦቴ ተሽከርካሪ ባለቤቶች፤ ተቀባይ ማደያዎች እና አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ በቀን 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሊትር ቤንዚን እንደሚያስፈግ የተገለጸ ሲሆን ባለፈው አንድ ወር በእያንዳዱ ቀናት 1 ነጥብ 43 ሚሊየን ሊትር እንደገባ ተገልጻል።
ይህ ቁጥር ከፍላጎቱ አንጻር ተመጣጣኝ ቢሆንም በህገ ወጥ መልኩ የሚሰሩ አካላት ግብይቱ ላይ በመኖራቸው ማህበረሰቡ አሁንም እንዲጉላላ እያደረጉ መሆናቸውን በማንሳት እነዚህ ላይ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ