ታኅሳስ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢፌዴሪ አየር ሃይል ዋና አዛዡ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይሉ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የስራ እና የግዳጅ አፈፃፀም እንቅስቃሴዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተናገሩ።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በየዘመናቱ ሁሉ የተሰጡትን ሃገራዊ ግዳጅ እና ተልዕኮዎችን በአስተማማኝ ብቃት እየተወጣ ዛሬ ላይ የደረሰ በድል እና በመስዋዕትነት የደመቀ አኩሪ ታሪክ ያለው አንጋፋና ስመ ገናና የአቭዬሽን ተቋሙ መሆኑን ገልጸዋል።
አየር ሃይሉ አሁንም ዘመኑን በዋጀ መልኩ ተደራጅቶ የኢትዮጵያን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል በ2022 ከአፍሪካ ቀዳሚ ተመራጭ የአቭዬሽን ተቋም ለማድረግ የተያዘውን ራዕይ በትክክለኛው መስመር እየተጓዘ መሆኑን ያስታወቁት ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የኢትዩጵያ አየር ኃይል በአሁኑ ወቅትም ሀገራችንን ከውጭም ሆነ ከውስጥ የጥፋት ቡዱኖች ለመከላከል በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ መናገራቸውን መከላከያ ሰራዊት ዘግቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ