👉 የበዓል ስራዎቸን በሚከናወኑበት ጊዜ ሁሉንም ስራዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከማከናወን መቆጠብና ስራዎችን በቅድመ ተከተል እንዲሁም እንደቤተሰብ አባል ብዛትና ችሎታ ስራን መከፋፈል ያስፈልጋል።
👉በአንድ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ላይ ሶኬቶችን ደራርቦ አለመጠቀም ፣ ጋዝ ሲሊንደር ከመለኮስዎ በፊት በጋስ ሲሊንደር መስመር ዉስጥ ያፈተለከ ጋዝ አለመኖሩን ማረጋገጥ ።
👉 ከሰል በመጠቀም ጊዜ የከሰል ምድጃዉን ከቤት ዉጪ በማድረግ ከሰሉ ጢሱን እንዲጨርስ ማድረግና ወደቤት ካስገቡ በኋላም በርና መስኮት በመክፈት በቂ የአየር ምልልስ እንዲኖር ማድረግና ስራዎን ካጠናቀቁ በኋላም ምድጃዉን ከቤት በማዉጣት እሳቱን በዉሀ በማጥፋት ቤቱን ማናፈስ።
👉ለክብረ በዓሉ ወይም ለብርሀን አገልግሎት የለኮሱት ሻማ ከመጋረጃና ከሶፋ እንዲሁም ከሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ጋር እንዳይገናኝ ጥንቃቄ ማድረግና ከመተኛትዎ በፊት ወይም ከቤት በሚወጡ ጊዜ የለኮሱትን ሻማ ማጥፋትዎን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
👉በንግድ ማዕከላትም ነጋዴዎች የንግድ ሱቆቻቸዉን ዘግተዉ ከመዉጣታቸዉ በፊት የተዘነጉ የኤሌክትሪክ ሶኬቶችን እና የተለኮሱ ሻማዎች ካሉ መጥፋታቸዉንና መቋረጣቸዉን ማረጋገጥ ።
ከላይ የተጠቀሱትንና መሰል የጥንቃቄ ተግባራትን በመፈጸም በዓሉ ያለአደጋ ክስተት በሰላም እንዲያልፍ አደጋን አስቀድሞ በመከላከል ኃላፊነትዎን እንዲወጡ ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።
ከዚህ አልፎ ለሚያጋጥሙ ማናቸዉም አደጋዎች ኮሚሽን መ/ቤቱ አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት ያደረገ መሆኑን ገልጾ ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁ ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ እንዲያሳውቁ ገልጿል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ