ታኅሳስ 29 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቻይና ተራራማ አካባቢ ማክሰኞ ማለዳ በደረሰ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 95 ሰዎች መሞታቸውን እና 130 ጉዳት እንደደረሰባቸው ቢቢሲ ዘግቧል።
በቲቤት ቅዱስ በምትባለው ሺጋቴሴ ከተማ በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር ጠዋት ሦስት ሰዓት አካባቢ የደረሰው ርዕደ መሬት በሬክተር ስኬል 7.1 መጠን ያለው ሲሆን፣ 10 ኪሎ ሜትር ጥልቀት እንደነበረው የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ አመላክቷል።
ጉዳትን ካደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ በአካባቢው በርካታ ተከታታይ ንዝረቶች መሰማታቸው ተመላክቷል።
የመሬት ነውጡ የፈጠረው ንዝረት የቻይና አጎራባች በሆኑት በኔፓል እና በተወሰኑ የሕንድ ግዛቶች ውስጥ ተስምቷል።
አደጋው የደረሰበት የቻይና ክፍል በተደጋጋሚ የመሬት ነውጥ የሚከሰትበት ሲሆን፣ አካባቢውም ከፍተኛ ሥነ ምድራዊ እንቅስቃሴዎች የሚታዩበት መሆኑ ተነግሯል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
011-639-28-52
011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት radio 99.1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube
ምላሽ ይስጡ