ታኅሳስ 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዋሽ ፈንታሌ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በከሰም ስኳር ፋብሪካ አካባቢ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል፡፡
በአፋር ክልል የመንግስት ልማት ድረጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሰን ዳውድ እንዳስታወቁት፣ በአካባቢ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል፣ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችና ተቋማት ላይም ጉዳት እያደረሰ ይገኛል ብለዋል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጡ ከመጠነኛ ከፍ ወዳለ ደረጃ እየተሸጋገረ መምጣቱን ተከትሎ በአካባቢው በመኖሪያ ቤቶችና መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ያሉት አቶ ሀሰን፤ በተለይ ከትላንት ጀምሮ የነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳቱን ከፍ እያደረገው እንዳለ ጠቁመዋል፡፡
እስካሁን በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው አደጋ ባይኖርም የስኳር ፋብሪካውን ጨምሮ በአካባቢው ባሉ ማህበረሰቦች መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት፡፡ ይሁን እንጂ በአካባቢው የከሰም ግድብ እስካሁን ባለው ሁኔታ ጉዳት እንዳልደረሰበት ጠቁመዋል፡፡
ንዝረቱ አሁንም እየቀጠለ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ዜጎችን ከአካባቢው የማስወጣት ሥራ በስፋት እየተሰራ እንዳለ አስታውቀዋል፡፡ የከሰም ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞችም ከአካባቢው እየወጡ እንዳለ ተናግረዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ትላንት ሌሊት 9:53 ሰዓት ላይ ከሰሞኑ በመጠኑ ከፍ ያለና ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ይታወቃል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ