ታኅሳስ 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ ያለውን ግጭት በሽምግልና ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትላንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ባለፈው ሳምንት ግጭቱ መከሰቱን ሰምተናል በማለት ጉዳዩ በአጎራባች ባሉ ሽማግሌዎች እንዲፈታ ውይይት እየተደረገበት ስለመሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው እንዳሉት፣ የአካባቢውን ሰላም በጋራ ለማስከበር ኢትዮጵያ ከኢጋድ አባል ሀገራት ጋር ሁሉ እየሰራች መሆኑን ጠቅሰዋል። መሰል ድርጊቶች ዳግመኛ እንዳይከሰቱ ንግግሮች በሽማግሌ ተይዘዋል ሲሉም ገልጸዋል።
አሁን ላይ በአካባቢው ጊዜያዊ ሰላም መስፈኑን በመጥቀስ በቀጣይም አካባቢው ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ይደረጋል ሲሉ አምባሳደር ነቢያት ተናግረዋል። ግጭቱ ዶሎው በምትሰኝ የሶማሊያ ከተማ ሰፍረው በነበሩ የሶማሊያ ወታደሮችና በኢትዮጵያ ወታደሮች መካከል እንደነበር ይታወሳል።
ባለፈው ሳምንት የሶማሊያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ በሶማሊያ መንግሥት ኅይሎች ሥር በነበሩ ሶስት ይዞታዎች ላይ የኢትዮጵያ ኅይሎች ጥቃት ፈጽመዋል ማለቱ ይታወሳል። ድርጊቱ የአንካራውን ስምምነት የጣሰ ነው ስትልም ሶማሊያ ማስታወቋ ይታወቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ