ታኅሳስ 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ግብፃዊው ኮኮብ ፍርኦኑ ሞ ሳላህ ዘንድሮ አይቀመሴ አቋም ላይ ነው የሚገኘው። በወርሀ ታኅሳስ ብቻ በ7 ጨዋታ 7 ጎል በሊጉ 17 ጎል በማስቆጠር 13 ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። ይህንን ለማድረግ 18 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ብቻ ነው የጠየቀው ተጫዋቹ ያለበትን አቋም በደንብ የሚያሳይ ጉዳይ ነው።
ታዲያ ከክለቦች ትልቁ የውድድር መድረክ የሆነው ባለ ትልቅ ጆሮው የሻምፓዮንስ ሊግ ዋንጫ ይልቅ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ዘንድሮ ማሳካት እንደሚፈልግ ተናግሯል። ቀጣይ አመት ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም ፤ ዘንድሮ በጣም ያስፈልገናል ፤ ከዚ በፊት አሳክተነዋል ግን ጊዜው Vovid ስለነበረበረ አደብዝዞታል ግን የዘንድሮውን ከደጋፊዎቻችን ጋር በጋራ አሳክተን ማክበር ነው የምፈልገው ሲል ግብፃዊው ኮኮብ ሀሳቡን ሰጥቷል።
አያይዞው ስለ አሰልጣኝ አርን ሽሎት ሀሳብ ሰጥቷል። ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ቡድኑን ከአርን ሽሎት ተረክቦ አመርቂ እንቅስቃሴን እንዲያደርጉ ምክንያት ነው። ታዲያ ሞ ሳላህ መጀመሪያ እኔም ቡድኑን በዚ ደረጃ ያዋቅረዋል ብዬ አልጠበኩም የክሎፕ Legacy በጣም ትልቅ እና ደጋፊዎችም ብዙ ነገር ስለሚጠብቁ ያንን እንደወረደ ማድረግ ይችላል የሚለው ጥርጣሬ ነበር ለኛም ግን ከጠበኩት በላይ ነው በጣም ብርቱ እና ጎበዝ አሰልጣኝ ነው ሲል ስለ አርን ሽሎት መስክሯል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ