ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በመዲናችን አዲስ አበባ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚካሄደው ኤክስፖው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ፤ ከሙዚቃ እና ከአልኮል ነጻ በሆነ መልኩ በኤግዚቢሽን ማእከል እንደሚከናወን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
በማርኮናል ኤቨንት ኦርጋናይዘር እና በኬብሮን የዝግጅት አጋፋሪዎች የተዘጋጀው ኤክስፖው ‹‹አብሮነት ለእድገት በሚል መሪ ቃል››ከጥር 3 -9 ቀን 2017 በተከታታይ ለሰባት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የንግድ እና ባዛር ትርኢቱ በአደባባይ በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ በሃገራችን የሚኖረውን የቱሪስት ፍሰት ተከትሎ ባህል እና የበዓሉን ሃይማኖታዊ አከባበር በኤክስፖው ለማሳየት ያለመ መሆኑን የማርኮናል ኤቨንት ኦርጋናይዘር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም አደፍርስ ገልጸዋል።
ሃይማኖታዊ ትውፊቱን በጠበቀ ሁኔታ ከሙዚቃ እና ከመጠጥ ነጻ በሆነ መልኩ የሚካሔደው የንግድ ትርኢትና ባዛሩ በመንፈሳዊ ዝማሬዎች እና በኪነ-ጥባብዊ ውድድሮች መካሄዱ ለየት የሚያደርገው መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በኤክስፖው የንግድ እንቅስቃሴ ላይ የማንኛውም አይነት ሃይማኖት ተከታይ በተመጣጣኝ ዋጋ መሳተፍ የሚችል መሆኑ የገለጹት የኬብሮን ዝግጅት አጋፋር ዋና ስራ አስኪያጅ ዲያቆን ቃለስብሃት ዘመረ ነገር ግን በህትመት ደረጃ እና ሌሎች ሃይማኖታዊ ማስታወቂያዎች መጠቀም የተከለከለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ጥር 3 ቀን 2017 በሚከፈተው የጥምቀት ኤክስፖ ከ150 በላይ ተሳታፊዎች እና ከ10 ሺ በላይ ጎብኝዎች ይመጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከኤክስፖው የሚገኘው ገቢ ለተለያዩ የመርጃ ማዕከላት እና ገዳማትን ለመደገፍ እንደሚውል አዘጋጆቹ ተናግረዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ