ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሳህል ቀጠና እና የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች ለሰላም እና መረጋጋት አፅንኦት እንዲሰጡ የኬንያው ፕሬዝዳንት ጠይቀዋል፡፡
የአፍሪካ መሪዎች አዲሱን የፈረንጆች ዓመት የሰላም እና አንድነት እንዲያደርጉ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ በሃገራቱ እና ቀጠናው በሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ላይ በመስራት በ2025 መረጋጋት እና ትብብር እንደሚኖር ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እ.ኤ.አ በ2024 ኬንያ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮች እና የጸጥታ ስጋቶች እንዳጋጠሟት አምነዋል።
የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማሻሻል እና የህዝብ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዜሽን በማድረግ ውጤታማነትን ለማሻሻል መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት አመልክተው በመላው አፍሪካ ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ አቅርበዋል።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ እየተካሄደ ባለው የሰላም ድርድር መሪዎች ከፖለቲካ ይልቅ ለአንድነትና ለሰላም ቅድሚያ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።
የኒጀር ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብዱራሃማኔ ቲያኒ ደግሞ “እራሳችንን ለመጠበቅ የሳህል መንግስታት ኮንፌዴሬሽን ህብረትን አቋቁመናል” ሀገሪቱ በምዕራብ አፍሪካ እና በአለም ዙሪያ መልካም ጉርብትና ግንኙነት ለማድረግ ትሰራለች ሲሉ ቃል ገብተዋል። ዜጐች የሀሰት መረጃ ስርጭትን እንዲከላከሉ እና ባህላዊ እሴቶችን እንዲያስከብሩ እንዲሁም የውጭ ተጽእኖዎችን በንቃት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
የናሚቢያው ፕሬዝዳንት ናንጎሎ ምቡምባ በሱዳን፣ በሳህል እና በምስራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰላም እንደሚሰፍን ተስፋ አድርገዋል። “ናሚቢያ ፍትህን፣ አንድነትን እና ሰላምን ፍለጋዋን ትቀጥላለች” ሲሉ ሀገሪቱ ለአለም አቀፍ ግጭቶች ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለመስጠት ቁርጠኝነቷን ገልጻለች ሲል አናዶሉ ዘግቧል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ