ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያና ሶማሊያ አልሻባብን በጋራ ለመዋጋት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ኢትዮጵያና ሶማሊያ ባለፉት ጥቂት ቀናት በአዲስ አበባ እና በሞቃዲሾ ምክክር ያደረጉ ሲሆን ከተወያዩባቸው ቁልፍ ጉዳዮች መካከል አልሻባብን በጋራ መዋጋት ዋነኛው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በወቅታዊ፣ አከባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የተመራው ልዑክ በቅርቡ በጂቡቲ እና በኬንያ እንዲሁም በመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የተመራ ልዑክ በሶማሊያ ጉብኝት ማድረጉንና በበርካታ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን ቃል አቀባዩ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮን(African Union Support and Stabilization Mission) የሰላም አስከባሪ ኃይል መመለስ ስለመቻሏ ለተነሳላቸው ጥያቄ ቃል አቀባዩ ውይይት እየተካሄደበት ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በቅርቡም የሁለቱን ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያካተተ ውይይት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሰራዊት ከ21 አመታት በላይ በሶማሊያ ሰፍሮ ከአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሃይል ጋር በመሆን አፍሪካዊና ቀጠናዊ ተልዕኮውን ሲወጣ መቆየቱ ይታወቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ