ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) መጪውን የገና በዓል አስመልክቶ በሚደረገው ግብይት ህገ ወጥ የንግድ እና የማጭበርበር እንቅስቃሴ እንዳያጋጥም ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
ይህንን ተከትሎም በመዲናዋ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግባቸውን ሁኔታዎች ለመቀነስ እንዲሁም በድርጊቱ የሚሳተፉ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን ኮሚሽኑ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
አዲስ አበባ በርካታ የንግድ እቅስቃሴ የሚከናወንባት ከተማ እንደመሆኗ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች በበዓላት ወቅት በስፋት እንደሚስተዋሉ የገለጹት የኮምሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ በጸጥታው በኩል አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል፡፡
በተለይም መደበኛ በሆኑ የመገበያያ ስፍራዎች እና ባዛሮች ላይ ሃሰተኛ የብር ኖቶችን በመጠቀም ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን የሚያከናውኑ አካላት በመኖራቸው ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የሚያግዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ህብረተሰቡም ዲጂታል የመገበያያ አማራጮችን መጠቀም በሃሰተኛ የብር ኖቶች የሚከናወኑ ህገ ወጥ ድርጊቶችን እንዲከላከል ጠይቀዋል፡፡
ሃሰተኛ የብር ኖቶች ለመገበያያነት እንዳይውሉ ነጋዴው ማህበረሰብ በግብይት ወቅት የብር ኖቶትችን የማረጋገጥ እንዲሁም ሸማቹ ማህበረሰብም ገንዘብ ሲቀበልም ሆነ ሲሸምት ይህን ከግምት በማስገባት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ብለዋል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባና መሰል ህገ ወጥ ድርጊቶች በሚያጋጥም ወቅት በአቅራቢያው ለሚገኝ የህግ አካል በማሳወቅ ሃላፊነቱን እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ አሳስበዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ