ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጪው የገና በዓል በሚከናወን እርድ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ምርምር ልማት ማዕከል ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ማዕከሉ ከፍተኛ የሚባል የቆዳ ውጤቶችን የሚሰበሰበው በበዓላት ወቅት እንደሆነ የሚናገሩት የማዕከሉ የቆዳ ኢንዱስትሪ ግብዓት ዴስክ ሃላፊ አቶ ታረቀኝ ጂዳ፤ እርዱን የሚያከናውኑ አካላት ከስጋው ባሻገር ለቆዳው ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
በአገሪቱ የሚስተዋለው የጥሬ ቆዳና ሌጦ የጥራት ችግር የምርቱ ዋጋ በዓለም ገበያ እንዲያሽቆለቁል በማድረጉ በውጭ ምንዛሪ ገቢ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ አስታውቀዋል፡፡
የጥሬ ቆዳና ሌጦ የጥራት ችግሩ እንስሳቱ በህይወት እያሉ፣ በእርድ ወቅትና ከእርድ በኋላ በሚፈጠሩ ችገሮች ምክንያት የሚከሰት መሆኑን የሚያነሱት ኃፊው በእርድ ወቅትም በቸልተኝነት በቆዳው ላይ የሚፈጠሩ ቀዳዳዎች ቆዳውን ከጥቅም ውጭ እያደረጉ በመሆኑ ህብረተሰቡ በበዓል ወቅት እርድ ሲያከናውን ለቆዳ ጥራት እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል፡፡
በበሬ ቆዳ ላይ በቅርጫ ወቅት አጥንት የመከስከስ ሁኔታ ቆዳን እየጎዳ መሆኑንም የቆዳ ኢንዱስትሪ ግብዓት ዴስክ ሃላፊ አቶ ታረቀኝ አመላክተዋል፡፡
የቆዳና ሌጦ ውጤቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ጭምር ትልቅ አስተዋጽዖ ያለው መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ ኢትዮጵያ የምታገኘውን የቆዳ ሃብት በአግባቡ መጠበቅ ይገባል ብለዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ