ታኅሳስ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን አዶላ ወዮ ከተማ የሚገኘውን ስታድየም ለማሳደስ ገቢ ሊሰባሰብ መሆኑን የአዶላ ወዮ ከተማና አካባቢዋ ተወላጆች በጎ አድራጎት ድርጅት አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ በሰጠው መግለጫ በዞኑ በርካታ ስመጥር ሯጮች፤እርግ ኳስ ተጫዎቾችና ሌሎችም አንጋፋ ሰዎች በወጡበት ከተማ ከጥር 3እስከ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በከተማዋ ስፖርታዊ ውድድሮችና ባህላዊ ክዋኔዎች ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡
የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ ፖለቲከኛ አቶ አበበ አካሉ እንዳሉት በ1977 ዓ.ም በከተማዋ የተመሰረተው ስታድየም አሁን ላይ በእርጅና ምክንያት የዘመኑን ትውልድ ስፖርታዊ ፍላጎቶች ማሟላት አልተቻለም፡፡
አክለውም በዞኑ ለዓመታት ወርቅ በማውጣት ከሚሰራው ሜድሮክ ድርጅት ጀምሮ የከተማዋ አስተዳደር ፤የአካባቢው ተወላጆች የክልሉ መንግስትና ሌሎችም ጉዳዩ ሚመለከታቸው አካላት ለስታድየም እድሳቱ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡የአዶላ ወርቃማው ሩጫ በሚል ስያሜ የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡
የአዶላ ወዮ ከተማና አካባቢዋ ተወላጆች በጎ አድራጎት ድርጅት ከዚህ ቀደም በየአመቱ ለተማሪዎች እና ለአቅመ ደከማዎች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ከስታድየሙ ባሻገር ትውልዱ የሚታነፁበት ቤተ መፅሀፍት ለመገንባት መታቀዱ ተገልጿል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ