ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ ዲጂታል ፋይናንስን ለማስፋፋት ካቀደው እቅድ ቀድሞ ማሳካት መቻሉን አመላክቷል፡፡
የዲጂታል ስርዓቱ መስፋፋት በአገልግሎት አሰጣጥ ሒደት የሚታየውን ክፍተት የሚቀርፍ፤ የባንኩንም ወጪ የሚቀንስ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ተናግረዋል፡፡
እ.ኤ.አ በ2026 የባንኩን ተቀማጭ ሀብት 1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ለማድረስ ታቅዶ፤ አሁን ላይ እቅዱን ማሳካት እንደተቻለ ገልጸዋል፡፡
አሁን ላይ የባንኩ ተቀማጭ ሀብት 1 ነጥብ 97 ትሪሊየን መድረሱን ፕሬዚደንቱ አመላክተዋል፡፡ አጠቃላይ የባንኩን ሀብትም 1 ትሪሊየን 419 ቢሊዮን ማድረስ መቻሉንም አስረድተዋል፡፡
ባንኩ የመንግስት የልማት ድርጅት ቢሆንም፤ ለግሉ ዘርፍ የሚያቀርበውን የብድር መጠን ከፍ በማድረግ ትልቅ አቅም መፍጠር መቻሉንም አቶ አቤ አስታውቀዋል፡፡
የባንኩ የዳሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እና የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው ባንኩ ለበርካታ የልማት ድርጅቶች የፋይንስ አቅርቦት ተደራሽ በሚያደርግበት ወቅት የልማት ድርጅቶቹ እዳቸውን በአግባቡ ባለመመለሳቸው የተነሳ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ ገብቶ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡
ይሁን እንጅ አሁን ላይ መንግስት በሀገሪቷ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እዳውን ወደ ገንዘብ ሚኒስቴር በማዞር ከበጀት እንዲከፈል ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
ይህም ውሳኔ የባንኩን አቅም ለማሳደግ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በዓለም ባንክ ፕሮግራም ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬን ሚኒስቴሩ ለባንኩ የሚያቀርብለት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ባንኩ እቅዶቹን ለማሳካት ለ1 ወር የሚቆይ የደንበኞች አገልግሎት ወር መርሃ ግብርን በትላንትናው እለት አስጀምሯል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ