ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጤና ሚኒስቴር የማህበረሰቡን ጤና ለማሻሻል በተለይም የእናቶችን፣ ህጻናት እንዲሁም የጨቅላ ህጻናት ህመም እና ሞት ለመቀነስ ለድንገተኛ ህክምና አገልግሎት የሚውሉ 370 አምቡላንሶችን ለሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
በጤና ሚኒስቴር የመሰረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ አቶ እስክንድር ላቀው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአጋር ድርጅቶች በተለይም ከአለም ባንክ ባገኘው ድጋፍ 370 አምቡላንሶችን ለክልሎች በድጋፍ መልኩ ማስረከቡን ገልጸዋል።
በገጠሩ የሃገሪቱ ክፍሎች ባሉት አካባቢዎች ድንገተኛ አደጋዎች ሲያጋጥሙ እስከ ሆስፒታል ለመድረስ በሚደረግ ጥረት ያለውን እንግልት እና ስቃይ ለመቀነስ እንደሚረዳ አቶ እስክንድር ተናግረዋል።
በተጨማሪም እናቶች በወሊድ ጊዜ የሚገጥማቸውን ለሞት የሚያደርስ ስቃይ ያስቀራልም ብለዋል። በዚህም የጤና ስርዓቱን ተደራሽ ለማድረግና ለታለመላቸው እቅድ እንዲውሉ ከማድረግ አንጻር ክትትል እንደሚደረግም አክለው ገልጸዋል።
ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ ባለው ጊዜ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከ3ሺ14 በላይ አምቡላንሶችን ለፌዴራል እና የክልል ሆስፒታሎች ማከፋፈሉን አቶ እስክንድር አመላክተዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ