የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በትራፊክ ቅጣት በዓመት ከ17 ሚሊየን ብር በላይ የሚወጣውን ወጪ የሚያስቀር አዲስ ሶፍትዌር አስመረቀ
ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በኢንፍራቴክ የቴክኖሎጂ አበልፃጊ ድርጅት የበለጸገውን አዲስ ሶፍትዌር ባስመረቀበት መድረክ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚዴቅሳ፤ የትራፊክ ቅጣትንና የፓርኪንግ ክፍያን የሚያዘምን አዲስ ሶፍትዌር መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
ሶፍትዌሩ በአገሪቱ ብሎም በከተማዋ በማንዋል /በወረቀት/ በሚተገበር የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥር ስራ ላይ የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን እንደሚያስቀር ገልጸዋል፡፡
ወደ ተግባር ለመግባትም ዝግጅቱ መጠናቀቁን ያስታወቁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ቴክኖሎጂውን በይፋ በማስጀመር በትራንፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ሒደት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቅረፍ ቀልጣፋ አሰራር ለመዘርጋት ያስችላል ብለዋል፡፡
ሶፍትዌሩ የመንገድ ትራንስፖርት መቆጣጠሪያ ህግን መሰረት በማድረግ ግንዛቤ በመስጠት ቀልጣፋ የቁጥጥር ስራን ለማከናወን ይረዳል ነው ያሉት፡፡
ስራውን ከአሽከርካሪ እና ተሽከርካር ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፤ ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከባንኮች ጋር በማስተሳሰር እንደሚሰራ ያስረዱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ሲስተሙ ቀደም ሲል የነበረውን አሰራር በማዘመን በቁጥጥር ሒደት የሚያጋጥሙ ብልሹ አሰራሮችን የሚያስቀር ነው ብለዋል፡፡
ለትራፊክ ቅጣት በዓመት ከ17 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚወጣ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ሶፍትዌሩ ይህን ወጪ ያስቀራል ብለዋል፡፡
የትራፊክ ደንብን የሚተላለፉ አሸከርካሪዎች ታርጋቸው ሲፈታ እና መንጃ ፈቃድ ሲነጠቁ መልሰው ለመውስድ በሚደረግ ሒደት የሚያጋጥመውን መጉላላት የሚገታና በአጠቃላይ ከደንብ መተላለፍ የእርምት እርምጃ አወሳሰድ ጋር የነበሩ ሰው ሰራሽ ችግሮችን የሚቀርፍ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ ሲስተሙ ከፓርኪንግ አገልግሎት ክፍያ ጋርም የሚያያዝ በመሆኑ በፓርኪንግ አገልግሎት ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን እንደሚፈታ አስታውቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)

ምላሽ ይስጡ