ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የብስክሌት ትራንስፖርት ለማስፋፋት የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አ/ቶ ያብባል አዲስ ተናግረዋል ።እንደ ሀገር የብስክሌት ትራንስፖርት ለማስፋፋት የተጀመረው ሂደት ከፍተኛ ዉጤት ማስገኘቱንም አመላክተዋል፡፡
ቢሮው ለብስክሌት ትራንስፖርት የአደረጃጀትና የአሰራር ደንብ በማዘጋጀት ለከተማ አስተዳደሩ እንዲፀድቅ አቅርቦል ብለዋል።የቀረበው ደንብ በ1 ወር ውስጥ ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የቢሮው ሃላፊ ገልጸዉ የደንቡ መፅደቅን ተከትሎ የሚሰሩ የተለያዩ ስራዎች እንደሚኖሩ አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ከነፍ ኮሙኒኬሽን እና ኤቨንት ጋር በመተባበር‹‹ ብስክሌት በአዲስ›› የተሰኘ ወርሃዊ የብስክሌት ፌስቲቫል ሊጀመር መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ቢሮው የሞተር አልባ ትራንስፖርት ለማስፋፋት እና ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በዚህም የብስክሌት ትራንስፖርት በከተማዋ ተመራጭ እንዲሆን ለማስቻል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማጠናከር እና የግል ባለሃብቱ በዘርፉ እንዲሰማራ ማመቻቸት እንደሚገባ ሀላፊው ገልፀዋል።
በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ለሞተር አልባ ትራንስፖርት በተለይም ለብስክሌት ትራንስፖርት መስፋፋት ምቹ ሀኔታን መፍጠሩን የተናገሩት አቶ ያብባል መሰረተ-ልማቱን ከመጠበቅ እና ከመጠቀም፣ ከጤና፣ ከትራፊክ ደህንነት፣ ከከባቢ አየር ጥበቃ፣ ከቱሪዝም ዕሳቤ እና ከጊዜ አጠቃቀም አንጻር የብስክሌት ትራንስፖርት በከተማዋ ተመራጭ እየሆነ እንዲመጣ ዕድል ይፈጥራልም ብለዋል።
ፌስቲቫሉ በየወሩ በተመረጡ ቦታዎች ላይ የሚካሄድ ሲሆን ታህሳስ 27 ቀን 2017 ዓ.ም የመጀመሪያውን መርሃ-ግብር ከአደዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እስከ ራስ መኮንን ድልድይ ድረስ ለማካሄድ መታቀዱንም አስታውቀዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ