ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የቴሌኮም አግልግሎት ተደራሽነት አሁን ክፍተቶች የሚስተዋልበት መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት አመት በምክር ቤቱ ጥቆማ ተደርጎባቸው የነበሩ የተለያዩ ወረዳዎች እስካሁን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን አለመቻላቸውን የሚናገሩት አባላቱ በተደጋጋሚ አማራና አፋር ክልል እንደሁም አርጎባና ወላይታ አካባቢዎች በተደጋጋሚ በምክር ቤቱ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲደረግላቸው ቢጠየቅም እስካሁን ዝርጋታው አለመጀመሩን ተናግረዋል፡፡
የሃገሪቱ ድንበሮች አካባቢ ያለው የአገልግሎቱ ተደራሽት አሳሳቢ የሚባል መሆኑን ያነሱት አባላቱ በተለይም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ካላው የደህንነት ስጋት አኳያ የቴሌኮም አገልግሎቱ ውስንነት ያለበት በመሆኑ አገልግሎቱ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመለየት ማስተካከል እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን ተከትሎ ከሌሎች መሰረተ ልማቶች በፊት የቴሌኮም አገልግሎት መቋረጡ የዜጎችን አገልግሎት የማግኘት መብትን የሚጋፋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአገልግሎት ጥራት አና ተደራሽነት ለማሳደግ በቅድሚያ ተቋሙ ገቢውን ሊያሳድግ እንደሚገባ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ወጪው በራሱ የሚሸፍን መሆኑን የሚናገሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ በሚያገኘው ገቢ ልክ በእቅድ እደሚጓዝ አንስተው አገልግሎቱ ወጪውን ለማመጣጥ ሲል ለመሰረተ ልማት የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች በሃገር ውሰጥ ግብዓት በመሸፈን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ግጭቶች በሚስተዋልባቸው አካባቢያዎች አገልግሎቱ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል እንደማይቋረጥም ነው የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ የሚናገሩት፡፡
በቅርቡ በአገልግሎቱ ዋጋዎች ላይ የተሻሻሉ የክፍያ መጠኖች አገልግሎቱ ለሚሰራቸው የመስመር ዝርጋታዎች የሚያስፈልገውን 1.1 ቢሊዮን ዶላር ለመሸፈን እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ