ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቀይ መስቀል ማህበር ከተቋቋመበት ከ1927 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎች እና የልማት ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ሰብዓዊ ድርጅት እንደሆነ ይታወቃል።
ባለፉት አመታት በሃገሪቱ በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ሰበዓዊ የድጋፍ ስራዎችን ለማከናወን ወደ ተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የማህበሩ አባላት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በአባላቱ እንዲሁም በማህበሩ ንብረቶች ላይ የተለያየ ጉዳት እየደረሰባቸዉ መሆኑን የተናገሩት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰብዓዊ ዲፕሎማሲና የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ አቶ መስፍን ደረጄ ናቸዉ፡፡
ከሰሞኑም የማኅበሩ አምቡላንሶች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ እና በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ለህይወት አድን ተግባር በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ባልታወቁ ኃይሎች በተተኮሰባቸው ጥይት የሁለቱም አምቡላንስ አሽከርካሪዎች ለከፍተኛ ጉዳት የተዳረጉ ሲሆን አምቡላንስ ተሽከርካሪዎቹም ላይ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ መሰል ድርጊቶች እየቀነሱ ያሉ ቢሆንም አሁንም ድረስ በአባላቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አካላት በመኖራቸው ጥቃት አድራሾች ማህበሩ ከየትኛውም አካል ገለልተኛ ሆኖ እየሰራ ያለ ማህበር መሆኑን በመረዳት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ተቋሙ በማህበራዊ ድህረ ገጹ ባስታወቀው መረጃ መሰረት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሠራተኞቹን ጨምሮ በበጎፈቃደኞቹ እና ተሽከርካሪዎቹ ላይ በሚፈፀሙ ጥቃቶች አማካኝነት ሰብዓዊ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ወገኖች ለማድረስ ተግዳሮት እንደሆነበት ገልጿል።
የማኅበሩ ሠራተኞችም ሆነ በጎፈቃደኞች በነፃነት ተንቀሳቅሰው ሰብዓዊ ተግባራቸውን ማከናወን እንዲችሉ እና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ማኅበረሰቡም ድርጊቶቹን እንዲያወግዝ ጠይቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ