ታኅሳስ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአማራ ክልል በተከሰተው ድርቅ የከፋ ችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን የምግብ ድጋፍ መላኩን ገልጿል።
በአማራ ክልል ባለው ግጭት እና ተፈጥሯዊ ችግሮች ምክንያት በተለይ በሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ድርቅ እና የምግብ እጥረት ከ5 አመት በታች ያሉ ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸው ታዉቋል።
በተከሰተው ረሃብ ምክንያት የከፋ ችግር ውስጥ ከሚገኙ 79 ሺህ ሰዎች መካከል 4 ነጥብ 5 በመቶ ለሚሆኑ ዜጎች የሚውል ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ፤ ከ550 በላይ ኩንታል የስንዴ ዱቄት እና 3 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት ድጋፍ መላኩን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታውቋል።
የተላከው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ ድጋፎችን ለማድረግ የችግሩን ጥልቀትና መጠን ማወቅ እንዲቻል ጥናት የሚያደርጉ ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን የተናገሩት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰብዓዊ ዲፕሎማሲና የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ አቶ መስፍን ደረጄ ናቸዉ፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ 79 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው እና ከነዚህም መካከል ህጻናት በይበልጥ ተጎጂ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ የድጋፍ ስራዎችን ለማከናወን መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን የማስተባበር ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ሃላፊው ገልጸዋል።
የጥናቱ ውጤት ሲጠናቀቅ ተባባሪ ለሆኑ አጋር ድርጅቶች የጉዳቱን መጠን በማሳየት የድጋፍ ጥሪ የማቅረብና ተጨማሪ የምግብ፤ የመድሃኒት እና መሰል የድጋፍ ስራዎች ተጠናክረው እንደመሚቀጥሉ ተመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ