ታኅሳስ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢፌዴሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን በ2017 ዓ.ም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ስልጠና መስኮቻቸውን በአዲስ የፍቃድ አሰጣጥ ደረጃ መሠረት ለመገምገም እና እንደ ሀገር ወጥነት ያለው የፍቃድ አሰጣጥ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዳግም ምዝገባ እየተካሄደ እንደሆነ ይታወቃል ።
ባለፈው አመት የካቲት ወር ላይ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት መመሪያ እና ስታንዳርድ ፀድቆ ስራ ላይ የዋለ ሲሆን ፤ተቋማቱ በፀደቀው መመሪያ እና ስታንዳርድ እየሰሩ መሆናቸው ሲገመገም መቆየቱን የኢፌዴሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ማርታ አድማሱ ገልፀዋል።
ባለስልጣኑ በሚሰራው የማጣራት ሂደት ምዝገባውን እንዲያካሂዱ ጥሪ ከቀረበላቸው 102 ተቋማት 84 የሚሆኑት ምዝገባውን ባለማካሄዳቸው በገዛ ፍቃዳቸው ከመማር ማስተማር ስርዓቱ እንደወጡ ተናግረዋል፡፡
84 ተቋማት ከስርዓቱ አጠቃላይ ሪፖርታቸዉን በሚቀጥሉት 2 ሳምንታት ውስጥ ካላከናወኑ ፍቃዳቸው እንደሚነጠቅ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዋ አክለዉ ተናግረዋል፡፡ በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ዉስጥ የመውጫ ፎርም መሙላት ግዴታቸዉ እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡
የመውጫ ፎርሙን ባልሞሉ ተቋማት ላይ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ