ታኅሳስ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለአጠቃቀም ምቹ እና ቀላል በሆኑት የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ላይ የሚጋሩ የሕዝብን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ መረጃዎችን በሕግ ብቻ መቆጣጠር እንደማይቻል የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጿል።
ባለሥልጣኑ በሕግ የተሰጠው ኃላፊነት አጠቃላይ የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ቁጥጥር ማድረግ እና ለተጠቃሚዎች ተደራሽ የሚሆንበትን ሁኔታ መፍጠር መሆኑን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ ተናግረዋል፡፡
በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚተላለፉ ጎጂ መልእክቶች፣ ማጭበርበር እና ወንጀሎችን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም እንደ ሀገር ያሉት የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ላይ የግንዛቤ ክፍተት በሚፈጥሩት የተሳሳተ አረዳድ ማኅበራዊ እሴቶቻችንን የሚያጎድፍ፣ ሰብአዊ መብት የሚጥስ እንዲሁም በሕግ ቁጥጥር ለማድረግ ጊዜ የሚወስድ እና አስቸጋሪ ስለሆነ የሚያደርሰውን ጉዳት በሕግ መቆጣጠር አዳጋች መሆኑን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከት የመጣው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች የጥላቻ ንግግር እንዲሁም ሃገራዊ እሴቶችን ያልጠበቁ ድርጊቶች እንደሀገር አሳስቢ ቢሆኑም ሕግ ሊፈታው ከሚችለው በላይ እንዲሆን ያደረገው በሁሉም ሰው እጅ የሚዘወር በመሆኑ ነዉ ብለዋል፡፡
ይህን ማስተካከል የሚቻለዉ ከህግ ቁጥጥር ባሻገር እንደ ሃገር ያለንን የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም መፈተሸና ግንዛቤን ከፍ ማድረግ ላይ በመስራት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
እንደ ሀገር ትውልድ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ዘመኑ ያበረከተውን የማኅበራዊ ሚዲያ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለተገቢ ነገር ለማዋል ሁሉም የሚመለከተው በመሆኑ፣ በጋራ ግንዛቤ መጨመር እና ለተገቢ ነገር መተርጎም ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሩ ኢንጂነር ባልቻ ሬባ አመላክተዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ