ታኅሳስ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጭዎቹ ሳምንታት የሚከበሩትን የገና እና የጥምቀት በዓላትን አስመልክቶ የደንበኞችን ፍላጎት መሠረት በማድረግ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ወደሚገኙበት ላሊበላ እና ጎንደር ከተማ የሚያደርገውን በረራ እንደሚያሳድግ አስታውቋል፡፡
አካባቢዎቹ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚመጡ ጎብኝዎች በስፋት የሚታደሙባቸው በመሆናቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር በረራን በበቂ ሁኔታ በማቅረብ የተለመደውን የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
ተጨማሪ በረራዎች ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ያለምንም መንገደኛ መሆኑን ተከትሎ ታሳቢ ያደረገ የዋጋ ማስተካከያ እንደሚደረግና የዋጋ ማስተካከያው ግን ወደ ከተሞቹ የሚደረጉትን መደበኛ በረራዎች የማይመለከት ነው ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ